Etiópia, Ethiopian Reporter, Amárico

[ad_1]

በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2023 ለመከላከያ ኃይል የዋለው ወጪ 2.4 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑን የስቶኮልም ዓለም አቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም አስታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1949 የተቋቋመውና በየዓመቱ ለውትድርና የዋለውን ወጪ የሚቃኘው ተቋም፣ ሰኞ ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በለቀቀው ሪፖርት፣ በ2023 ለወታደራዊ ወጪ የዋለው ገንዘብ ከዓለም ጠቅላላ ምርት በ2.3 በመቶ፣ ከ2022 ደግሞ በ2.2 በመቶ የበለጠ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

አዲስ ሪከርድ ያስመዘገበው ዓለም አቀፉ የአገር መከላከያ ወጪ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በዓለም በ2023 ለወታደራዊ ወጪ የዋለው ገንዘብ 2.4 ትሪሊዮን ዶላር ነው (ጌቲ ኢሜጅ)

ይህም በዓለም ላይ የሚኖሩ እያንዳንዳቸው ወንዶች፣ ሴቶችና ሕፃናት በአማካይ 306 ዶላር ለወታደራዊ ወጪ ታክስ ተደርገዋል የሚለውን ያሳያል ብሏል፡፡ ይህም ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ትልቁ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

– Advertisement –

Video from Enat Bank
Youtube Channel.

ለወታደራዊ ወጪ የዋለው ገንዘብ መጨመር፣ በዓለም ከተመዘገበው የ6.8 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር እንደሚዛመድም አክሏል፡፡

ለወታደራዊ ወጪ የሚውለው ገንዘብ በዓለም በሚገኙ አገሮች በሙሉ እኩል እንዳልሆነ፣ የዓለም ወታደራዊ ወጪያቸው ከፍተኛ የሆኑ አገሮች ጥቂት እንደሆኑም ጥናቱ አሳይቷል፡፡

አሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ ከሚያወጡ አገሮች በዓመቱ 916 ቢሊዮን ዶላር ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለወታደራዊ ወጪ ከዋለው 37 በመቶውን በማውጣት ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች፡፡ ቻይና 296 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት ስትከተል፣ ሩሲያ 109 ቢሊዮን ዶላር በማስመዝገብ በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡

ለወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የሚውለው ወጪ በተለይ የአውሮፓ አገሮች ከያዙት በጀት ጋር እንዳልተጣጣመ በጥናቱ ታይቷል፡፡

ዩክሬን የመከላከያ ወጪዋ 54 በመቶ ጨምሯል፡፡ ከአገሪቱ ጠቅላላ ምርት 37 በመቶ ወይም መንግሥት በጠቅላላ ካቀደው በጀት 60 በመቶ ያህል ለመከላከያ ወጪ መዋሉን ጥናቱ ገልጿል፡፡

ሩሲያ ወታደራዊ ወጪዋ በ24 በመቶ ሲያድግ፣ ይህም ከጠቅላላ ምርቷ 6.9 በመቶውን ይዟል፡፡ ከአገሪቱ ጠቅላላ የመንግሥት ወጪ ያለው ድርሻም 16 በመቶ ብቻ መሆኑንም ሪፖርቱ አክሏል፡፡

ሩሲያ በ2023 ለወታደራዊ ወጪ ያዋለችው ገንዘብ ሶቪየት ኅብረት ከ30 ዓመታት በፊት ከተበታተነች በኋላ ትልቁ በጀት ተብሎ የሚመዘገብ ነው፡፡ ሆኖም የሩሲያ ኢኮኖሚ በ22 በመቶ አድጓል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ወደ ውጭ የሚላከው የነዳጅና የኃይል አቅርቦት ኢኮኖሚው ችግርን እንዲቋቋም አድርጓል፡፡

ሃማስ በጥቅምት 2023 በእስራኤል ላይ የወሰደው ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ከመከላከያ በጀቷ የ24 በመቶ ጭማሪ ወይም 27.5 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከአጠቃላይ ምርቷ 5.3 በመቶውን ለመከላከያ እንድታውል አድርጓል፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ ወታደራዊ ወጪያቸውን ከጨመሩ አገሮች የተካተተች ሲሆን፣ የእስራኤልና የሳዑዲ ዓረቢያ የመከላከያ ወጪ በመካከለኛው ምሥራቅ ከተመዘገበው የበጀት ጭማሪ ዘጠኝ በመቶውን ይዟል፡፡

የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት፣ የሰሜን ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የአውሮፓ አባል አገሮች የድርጀቱን በጀት በ16 በመቶ እንዲጨምሩ አድርጓል፡፡

ፖላንድ ወታደራዊ በጀቷ በ7.5 በመቶ ሲጨምር፣ ከኔቶ አባል አገሮች የሩሲያን ረዥሙን ድንበር የምትጋራው ፊላንድም የመከላከያ በጀቷን በ54 በመቶ አሳድጋለች፡፡

የሰሜን አውሮፓና የባልቲክ አገሮች ወታደራዊ በጀታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር፣ እንግሊዝ 7.9 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

ጀርመን ከሌሎቹ አገሮች በተቃራኒ ወታደራዊ በጀቷን ላለመጨመር ስትታትር የከረመች ሆና ተመዝግባለች፡፡ የቀድሞዋ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጄላ መርከል እ.ኤ.አ. በ2021 ሥልጣን ሲያስረክቡ፣ የመከላከያ ወጪን ከአገሪቱ ጠቅላላ ምርት ከ1.33 በመቶ እንዳይበልጥ አድርገው የነበረ ሲሆን፣ የአገሪቱ መራሂተ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ ከአገሪቱ ጠቅላላ ምርት 1.5 በመቶ ለመከላከያ ወጪ እንዲውል አድርገዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ ወጪ እንዲጨር ምክንያት ከሆኑትም በዩክሬንና በሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት፣ የእስያ ጂኦፖለቲካዊ የፈጠረው ውጥረትና የመካከለኛው ምሥራቅ አለመረጋጋት ይጠቀሳሉ፡፡

2023 ከቀደሙት አራት ዓመታት ሲነፃፀር፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ የተመዘገበበት ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ሰዎችም የሞቱበት ነው፡፡ በዓለም በተለያዩ አገሮች በተከሰቱ ግጭቶችና ጦርነቶች ከ170 ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገው የክሪያሲስ ሞኒተሪንግ ግሩፕ ሪፖርት ያሳያል፡፡ 

[ad_2]

Source link

Notícias

Indonésia, Republika, Indonésio

[ad_1] REPUBLIKA.CO.ID, JAKARTA — Direktur Jenderal Bea dan Cukai Kementerian Keuangan Askolani buka suara soal tingginya sanksi administrasi barang impor. Dia menjelaskan besaran sanksi administrasi

Indonésia, Indo Pos, Indonésio

[ad_1] Harianjogja.com, DEPOK—Ombudsman Republik Indonesia (ORI) DIY meminta masyarakat untuk melapor jika menemui tiang-tiang kabel yang tampak semrawut. Laporan-laporan yang datang dari masyarakat ini akan

Hong Kong, South China Morning Post, Inglês

[ad_1] Hong Kong authorities will step up enforcement on illegal ride-hailing services and rogue taxi drivers over the coming Labour Day “golden week” holiday, while

Tailândia, Business Day News, Tailandês

[ad_1] มูลนิธิสุญญตาวิหารเผยหลักสูตรการดับทุกข์สำหรับผู้บริหารระดับสูงรุ่นแรก มีผู้สนใจในช่วงสองอย่างล้นหลาม รองประธานมูลนิธิฯเผยมีทั้งอดีตรัฐมนตรี อดีต สว. และอดีตปลัดกระทรวง สนใจ ชี้หลักสูตรนี้เหมาะกับโลกในยุคปัจจุบัน นายสมชาย เลิศด้วยลาภ รองประธานมูลนิธิสุญญตาวิหาร เปิดเผยว่าด้วยสถานการณ์ปัจจุบันสิ่งที่เกิดขึ้นทั้งในประเทศไทยและในโลก ทั้งปัญหาสังคม ปัญหาเศรษฐกิจ ปัญหาทุกอย่างอีกมากมายที่เกิดขึ้น สำหรับผู้บริหารจะมีการรับรู้และรับผิดชอบมากกว่าบุคคลทั่วไป ทั้งผู้บริหารหน่วยงานภาครัฐ และผู้บริหารหน่วยงานภาคเอกชน โดยทุกข์ที่เกิดขึ้นนั้น เกิดเพราะความรับผิดชอบที่มีต่อตัวเอง หน่วยงานและสังคม รวมถึงประเทศการเป็นทุกข์สำหรับผู้บริหารแล้ว มักจะไม่สามารถบอกหรือปรึกษาใครได้ เพราะความน่าเชื่อถือและความคาดหวังของคนในองค์กร