Etiópia, Ethioobserver, Inglês

[ad_1]

ሕፃን ልጅን በሞት እንደመነጠቅ መሪር ሐዘን የለም። ክፉና ደጉን ያለየ፣ ከእናትና ከአባቱ ውጭ ሰው ያለ ለማይመስለው ሕፃን፣ በዕድሜ የገፉ እንኳን ፈጽመው በሚጠሉት ሞት ከእናት እቅፍ መለየት ለሚሰሙት የሚያሳዝንለእናት ደግሞ የከፋ ሐዘን ነው። ማቲዎስ ወንዱ 1991 .ም. ተወልዶ 1996 .ም. በተወለደ አራት ዓመቱ ነበር በደም ካንሰር ሕመም ምክንያት ይችን ዓለም የተሰናበተው። የትኛውንም ክፉ ገጠመኝ ወደ መልካም ነገር ከቀየሩት ውጤቱ የተሻለና ለሌሎችም ጠቃሚ ነገርን ይዞ መምጣቱ አይቀርምና፣ የማቲዎስን መሞት ተከትሎ አባቱ አቶ ወንዱ በቀለና እናቱ / አምሳለ በየነ እንደማንኛውም ወላጅ በሐዘን ተኮራምተው እየተብሰለሰሉ መኖርን አልመረጡም፡፡ ይልቁንስ በስሙ በጎ አድራጎት ማኅበርን በመመሥረት በሺዎች የሚቆጠሩ ማቲዎሶችን ከካንሰርና ተያያዥ ከሆኑ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መታደግን ግባቸው አድርገው ተነሱ። 15 መሥራች አባላት ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ሚያዚያ 9 ቀን 1996 የመሠረቱት ማኅበር የዛሬው ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ በሥራዎቹ አምስት ዓለም አቀፍና ሁለት አገር አቀፍ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ በሶሳይቲው እንቅስቃሴ ዙሪያ አበበ ፍቅር አነጋግሯቸዋል።

ሪፖርተር፡ ድርጅታችሁ ላለፉት 20 ዓመታት ለምን ያህል ታማሚዎች ተደራሽ ሆኗል?

አቶ ወንዱ፡- ላለፉት ዓመታት  ከሦስት ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የካንሰር ሕሙማን የተለያዩ ድጋፎችን ያደረግን ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 86 ሕፃናትና 91 የማሕፀን በርና የጡት ካንሰር ሕሙማን ሴቶችን በመርዳት ላይ እንገኛለን። ከዚህ ባሻገር በተለይ ሴቶች የማሕፀን ጫፍና የጡት ካንሰር ተጠቂ ከመሆናቸው በፊት የግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ አበክረን እንሠራለን፡፡ በተመሳሳይ የትምባሆ ቁጥጥር ላይ ኅብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ  ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንገኛለን።

ሪፖርተር የካንሰር በሽታ በኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ማለት ይቻላል?

አቶ ወንዱ፡- የካንሰር ተጠቂዎችን ጨምሮ በሌሎች ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶች አሉት፡፡ አንደኛው የአመጋገብ ሥርዓታችን አለመስተካከል ሲሆን፣ ሌላው ትምባሆን ጨምሮ ሌሎች ለካንሰር የሚያጋልጡ ነገሮችን መውሰድ ነው። ከዚህ ባሻገር ብዙ ሰዎች በካንሰር የተያዘ ሰው አይድንም የሚል አጉል እምነት ስላላቸው በወቅቱ ወደ ሕክምና ተቋም አለመምጣት የታማሚዎችን ቁጥር ያበራክተዋል።

ሪፖርተር፡- ችግሩን ለማቃለል ድርጅታችሁ ምን እየሠራ ነው?

አቶ ወንዱ፡- ከአጋር ድርጅት ባገኘነው የገንዘብ ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር ባለሙያ በመቅጠር፣ ለሦስት ዓመት ከአሥር ወር ደመወዝ በመክፈል የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በአገራችን የመቆጣጠሪያ ዕቅድ እንዲኖራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገናል፡፡ በዚህም ዕቅድ መሠረት መንግሥት በመደበው በጀት በመቀሌ፣ በጎንደር፣ በጅማ በሐዋሳና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች የካንሰር ማዕከላት እንዲቋቋሙ፣ የአንዱ ዋጋ 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ስድስት ሬዲዮቲራፒ (የጨረር መሣሪያ) እንዲገዛ፣ ለማሕፀን በር ጫፍ ካንሠር በ1,300 የጤና ተቋማት ከሞላ ጎደል ነፃ የማሕፀን ጫፍ በር ካንሰር ምርመራና ሕክምና እንዲሁም 14 ዓመት ለሞላቸው ልጃገረዶች ነፃ የማሕፀን ጫፍ ካንሰር ክትባት እንዲሰጥ ሠርተናል፡፡

ሪፖርተር፡- የካንሰር ታማሚዎች ከሕክምናው ወጪ ባሻገር ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች ያስፈልጓቸዋል፡፡ እናንተ ከሕክምና በተጨማሪ የምታደርጉት ድጋፍ አለ?

አቶ ወንዱ፡- እውነት ነው፡፡ የካንሰር በሽታ እንደ ሌሎች በሽታዎች ቶሎ ታክሞ የሚድን አይደለም፡፡ በመሆኑም ብዙ የገንዘብ አቅም የሌላቸው ሰዎች ይቸገራሉ፡፡ እኛም ለእነዚህ  ሰዎች በመጀመሪያ ከአገራቸው የሚመጡበት ሙሉ የትራንስፖርት ወጪን የምንሸፍን ሲሆን፣ ከውጪ የሚገዙ መድኃኒቶች፣ ከሆስፒታል ውጪ በግል ተቋማት ለሚሠሩ ለላቦራቶሪ ምርመራ እንሸፍናለን፡፡ በሌላ በኩል ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ  ሕሙማንና  እየታከሙ ለሚማሩ ተማሪዎች ለአንዳንድ ወጪ መሸፈኛ በወር 1,000 ብር የምንሰጥ ሲሆን፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል 24 አልጋ ባለው የካንሰር ሕክምና ማዕከል ሙሉ የምግብ ወጪዎችን እንሸናለን።

ሪፖርተር፡- በቀጣይ ምን ለመሥራት አስባችኋል?

አቶ ወንዱ፡- ትልቁና የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ከፍለው የሚታከሙበትና የገንዘብ እጥረት ያለባቸው ደግሞ በድጎማ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ጤናማ አፍሪካ የተሰኘ ትልቅ የጤና ማዕከል መገንባት ነው። ማዕከሉ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ቅድመ መከላከልን መሠረት አድርጎ ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራን የሚሠራ መሆኑ ነው። ማዕከሉ ባለሀብቶችን በማስተባበር የሚሠራ ሲሆን፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች  ሕክምና አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ብለን እናስባለን።

ሪፖርተር፡- ድርጅታችሁ ለስንት ሰው የሥራ ዕድል ፈጥሯል?

አቶ ወንዱ፡- ሶሳይቲው ከ1,500 በላይ አባላትና 500 የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች አሉት፡፡ ወደ 30 ለሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቋሚ የሥራ ዕድልን ፈጥሯል፡፡ ስምንት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ነን፡፡ በየደረጃውም ከዚህ የተሻለ ለመሥራት አቅደናል።

ሪፖርተር፦ የማይተላለፉ በሽታዎች 52 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?

አቶ ወንዱ፡- እነዚህ ሕመሞች ብዙ ጊዜ ከዕድሜ መግፋት፣ ጤናማ ካልሆነ አመጋገብ፣ ያልተመጣጠነ የሰውነት ክብደት፣ ደካማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ትምባሆ፣ አልኮል መጠጦችና ጫት ከመጠቀምና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡ ሌላው ከዘመናዊ የአመጋገብ ሥርዓት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ለውፍረት ተጋላጭነት ይታያል። ይህ ደግሞ ለስኳር፣ ለደም ግፊት፣ ለልብ ሕመምና ሌሎች መሰል ችግሮች ይዳርገናል፡፡ በአገራችን የትምባሆ፣ ጫትና አልኮል መጠጥ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እየጨመረ ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ተደማምረው፣ በአገራችን ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አድርገዋል፡፡ በገዳይነት ቀዳሚ ከሚባሉት ውስጥ የሚገኘው የሳንባ ካንሰር ለምሳሌ ዋና መንስዔው ትምባሆ ነው፡፡ ሌላው በአገራችን በገዳይነት ከፍተኛ ደረጃ የያዘው የማሕፀን ጫፍ ካንሰር በልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት በሚተላለፍ ፓፒሎማ በተባለ ቫይረስ ምክንያት ሴቶች ላይ የሚመጣ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን ዝርዝር ጥናት ማድረግ ይጠይቃል፡፡

ሪፖርተር፡- ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ላይ ትልቁ ችግር የባለሙያ እጥረት እንደሆነ ይነሳል፡፡ እዚህ ላይ ምን ለመሥራት አስባችኋል? የመድኃኒት ሥርጭትን ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ምን እየተሠራ ነው?

አቶ ወንዱ፦ አትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ላይ በበቂ ሁኔታ ባለመሥራቷ በዓመት 31 ቢልዮን ብር ወይም 1.8 በመቶ የአገር ውስጥ ምርቷን ታጣለች፡፡ ስለዚህ በዋናነት መንግሥት በቂ ትኩረት እንዲሰጠው ግፊት እናደርጋለን፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ህንድ አገር ተጉዤ የነበረ ሲሆን፣ እዚያ ከሚገኝ የሕክምና ተቋም ጋር ባለሙያዎችን ማሠልጠን ስለሚቻልባቸው መንገዶች መክረናል፡፡ ምክንያቱም እንደ እኛ እምነት ከባለሙያ እጥረት ይልቅ እኛን የጎዳን ባለሙያው የተማረውን ተግባር ላይ ማዋል እንዳይችል ያሉበት ክፍተቶችና ማነቆዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ክፍያቸውና ጥቅማ ጥቅሞቻቸውም ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ በድህነት አቅሟ ብዙ አውጥታ ያስተማረቻቸው ባለሙያዎች የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በገፍ ወደ ውጭ አገር እየተሰደዱ ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ አገር የሸለመን ሰዎች ለሰዎች የሚባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ከ5,000 በላይ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ዶክተሮችና መሐንዲሶችን ያቀፈ ነው፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች በዓመት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ በፈረቃ ወደ አገራቸው እየመጡ ማገልገል ቢችሉ፣ ከዓመት እስከ ዓመት ያልተቋረጠና የተሟላ አገልግሎት መስጠት ይቻላል፡፡

[ad_2]

Source link

Notícias

Indonésia, Republika, Indonésio

[ad_1] REPUBLIKA.CO.ID, JAKARTA — Direktur Jenderal Bea dan Cukai Kementerian Keuangan Askolani buka suara soal tingginya sanksi administrasi barang impor. Dia menjelaskan besaran sanksi administrasi

Indonésia, Indo Pos, Indonésio

[ad_1] Harianjogja.com, DEPOK—Ombudsman Republik Indonesia (ORI) DIY meminta masyarakat untuk melapor jika menemui tiang-tiang kabel yang tampak semrawut. Laporan-laporan yang datang dari masyarakat ini akan

Hong Kong, South China Morning Post, Inglês

[ad_1] Hong Kong authorities will step up enforcement on illegal ride-hailing services and rogue taxi drivers over the coming Labour Day “golden week” holiday, while

Tailândia, Business Day News, Tailandês

[ad_1] มูลนิธิสุญญตาวิหารเผยหลักสูตรการดับทุกข์สำหรับผู้บริหารระดับสูงรุ่นแรก มีผู้สนใจในช่วงสองอย่างล้นหลาม รองประธานมูลนิธิฯเผยมีทั้งอดีตรัฐมนตรี อดีต สว. และอดีตปลัดกระทรวง สนใจ ชี้หลักสูตรนี้เหมาะกับโลกในยุคปัจจุบัน นายสมชาย เลิศด้วยลาภ รองประธานมูลนิธิสุญญตาวิหาร เปิดเผยว่าด้วยสถานการณ์ปัจจุบันสิ่งที่เกิดขึ้นทั้งในประเทศไทยและในโลก ทั้งปัญหาสังคม ปัญหาเศรษฐกิจ ปัญหาทุกอย่างอีกมากมายที่เกิดขึ้น สำหรับผู้บริหารจะมีการรับรู้และรับผิดชอบมากกว่าบุคคลทั่วไป ทั้งผู้บริหารหน่วยงานภาครัฐ และผู้บริหารหน่วยงานภาคเอกชน โดยทุกข์ที่เกิดขึ้นนั้น เกิดเพราะความรับผิดชอบที่มีต่อตัวเอง หน่วยงานและสังคม รวมถึงประเทศการเป็นทุกข์สำหรับผู้บริหารแล้ว มักจะไม่สามารถบอกหรือปรึกษาใครได้ เพราะความน่าเชื่อถือและความคาดหวังของคนในองค์กร